ጄንዋሪ 5 ቀን 2023

የመጀመሪያው የቦርድ ስብሰባና የሥራ ክፍፍል

የኢትዮጵያ ማህበር በቶሮንቶና አካባቢው ባለፈው ወር ማለትም ዲሴምበር 11 ቀን 2022
አገልግሎታቸውን በጨረሱ የቦርድ አባላት ምትክ አዳዲስ አባላት መምረጡ ይታወሳል፡፡
የቦርዱ የመጀመሪያ ስብሰባና የሥራ ክፍፍል ደግሞ ሀሙስ ጄንዋሪ 5 ቀን 2023 ተደርጓል፡፡ በዚሁም
መሰረት

1ኛ/ ወ/ሮ መሠረት ደመቀ ፕሬዚዳንት
2ኛ/ አቶ ዳዊት በየነ ም/ ፕሬዚዳንት
3ኛ/ አቶ እጹብድንቅ ለዓለም ጸሐፊ
4ኛ/ አቶ መስለ ገብረመድህን ገንዘብ ያዥ
5ኛ/ አቶ ደምሰው ተፈሪ ሕዝብ ግንኙነት
6ኛ/ ወ/ት ክበበ ወንጌል ወ/ማርያም አባል
7ኛ/ አቶ ታሪኩ የኋላእሽት አባል
8ኛ/አቶ ፈንታው አባተ አባል
9ኛ/ አቶ ብርሃኑ ሀብተገብርኤል አባል መሆናቸው ታውቋል፡፡

አዲሱ የቦርድ አመራር የስራ ክፍፍል ካደረገ በኋላ የወደፊት ሥራውን ለመቀጠል ከቀድሞው የቦርድ
አመራር የስራ ርክክብና ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎችንና እቅዶችን በጽሁፍ ርክክብ መደረግ እንዳለበት
አጽኖት በመስጠት በጽሁፍ አዘጋጅተው እንዲመጡ ተነጋግረው ስብሰባው ተጠናቋል፡፡

Similar Posts