ዲሴምበር 11 ቀን 2022

የኢትዮጵያ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ፤

ጊዜያቸውን በጨረሱ የቦርድ አመራር ምትክ አዳዲስ አስመረጠ

የኢትዮጵያ ማህበር ዲሴምበር 11 ቀን 2022 የዲሬክተሮች ቦርድ የጠራው ጠቅላላ ጉባኤ መካሄዱና እና ጊዜያቸውን በጨረሱ የቦርድ አመራር ምትክ አዳዲስ አባላት መመረጣቸው ተገለጸ፡፡

1950 ዳንፎርዝ አቬኑ በሚገኘው የማህበሩ ጽሀፈት ቤት ምድር ቤት አዳራሽ በተካሄደው ስብሰባ የማህበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ዓለማየሁ አስፋው ዓመታዊ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በማስከተልም የማህበሩ የፋይናንስ ኦዲትድ ሪፖርት በገንዘብ ያዡ በአቶ መሰለ ገበረመድኅን ሲቀርብ ገለጻ ደግሞ በማህበሩ አባል በሂሳብ ሙያቸው የሚረዱት አቶ ፍቅሬ ይታገሱ ተብራርቷል፡፡

የማህበሩ ሪፖርትና የሂሳብ ሪፖርት ከቀረበ በኋላ የንብረት ባለ አደራ ኮሚቴ ስብሳቢ አቶ ቢሹ ማሞ ዓመታዊ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

ከዚያም የሚቀጥለው ፕሮግራም ደግሞ ጊዜያቸውን በጨረሱ የቦርድ አመራር ምትክ ለማስመረጥ በተቋቋመው የአስመራጭ ኮሚቴ አማካኝነት 6 ሰዎች ለምርጫ ውድድር የቀረቡ ሲሆን፤ ከቤቱ ደግሞ የተወሰኑ ሰዎች ተጠቁመው አብዛኞቹ በሰራ መደራረብና በግል ምክንያት ጥቆማውን ባይቀበሉም አንድ ሰው ጥቆማውን ተቀብሎ ለውድድር ተጨማሪ 7ኛ ሰው በመሆን ምርጫውን ተሳትፏል፡፡ እንዲሁም

ወ/ት ክበበወንጌል ወልደማርያም(ሱዚ) በቦርድ አባልነት ቦርዱ አስገብቷት የቆየች ሲሆን በጠቅላላው ጉባኤ መጽደቅ ሰለነበረበት ጠቅላላ ጉባኤው አጽድቆ ወደ ተመራጮች ትውውቅና በመተዳዳሪያ ደንቡ መሰረት የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ተካሂዷል፡

አዲስ የተመረጡት የቦርድ አባላት

የምርጫው ውጤት ተቆጥሮ እስኪታወቅ ድረስ ተሰብሳቢው በማህበሩ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ የድምጽ አሰጣጡ ተቆጥሮ ወጤቱ ለአባላቱ ቀርቦ ሁለት ሰዎች ማለትም አቶ ዳዊት በየነና ወ/ሮ እመቤት መኮንን እኩል ድምጽ ሰላመጡ ቤቱ እንዲወስን አስመራጭ ኮሚቴው አቅርቦ ተመራጮቹ ለማህበሩ አገልግሎት ለመስጠት አንዱ አንዱን በመጋበዝና በቦርድ አባልነት እንዲቀጥል በፈቃደኛነት አንቺ ግቢ አንተ ግባ በመባባል ቅን ሃሳባቸውን ቢገልጹም፣ በቀድሞ አገልግሎትና በሥራ ልምድ አንጻር አቶ ዳዊት በየነ እንዲቀበሉ ቤቱ በጭበጨባ በሙሉ ድምጽ በመስጠቱ አቶ ዳዊት በየነ የቦርድ አባል ሆነዋል፡፡

የኢትዮጵያ ማሀበር የዴሬክተሮች ቦርድ

በዚሁም መሰረት የተመረጡት 9 አባላት እንደሚከተለው ነው፡፡ 1/አቶ ፈንታው አባተ 2/ ወ/ሮ መሰረት ደመቀ 3/ አቶ ብርሃኑ ሀብተገብሬል 4/ አቶ እጹብ ድንቅ ለዓለም ሽፈራው 5/ አቶ ዳዊት በየነ አዲስ የቦርድ አባል ሲሆኑ ከበፊቱ ቦርድ ደግሞ የቀጠሉት 6/ አቶ መሰለ ገብረመድኅን 7/ ወ/ት ክበበወንጌል ወ/ማርያም (ሱዚ) 8/ አቶ ደምሰው ተፈሪ 9/ አቶ ታሪኩ የኋላእሸት ናቸው፡፡

ሁሉንም የቦርድ አባላት መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን፡

Similar Posts